News
ኢንስቲትዩቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ፋከልቲ ጋር በመተባበር አህጉራዊ ስልጠና አዘጋጀ


ኢንስቲትዩቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ፋከልቲ ጋር በመተባበር ከግንቦት 15-20ቀን 2008 ዓ.ም ለአምስት ቀን የሚቆይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አስራ ስምንት የአፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ ተሳታፊዎች በሶሎቴ ሆቴል እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ፋካሊቲ/ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የተደገፈ ስልጠና እየተሰጠ ነዉ ፡፡
በብሔራዊ የሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የሳይንስ መሣሪያዎች ስልጠና እና ምክር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና የራፍ 0041 ሪጅናል ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት ኢንጂነር አበባየሁ ማሞ እንደገለፁት ስልጠናዉ በዋናነት የሚያተኩረዉ የኤክስሬይ እና ፍሎሮስኮፒ ማሽን አጠቃቀም እና ጥገና ላይ ነዉ ብለዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለዉም ሀገራችን ይህን መሰል ስልጠና ማዘጋጀቷ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለዉ ጠቅሰዉ አሁን እየተሰጠ ባለዉ ስልጠና ላይ ከሌሎች አፍሪካ ሀገራት አንድ ሰዉ ብቻ የሚሳተፍ ሲሆን ሀገራችን ግን አምስት ሰዎች በተጨባጭ ሀገራቸዉ ዉስጥ የመሰልጠን እድል ተፈጥሮላቸዋል ብለዋል፡፡ ከእዚህም በተጨማሪ ሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ የተለያዩ አሀጉራዊ እና አለማቀፋዊ ስልጠናዎችን የማዘጋጀት ልምዷን የበለጠ ከፍ እንደሚያደርገዉ እና ሰልጣኞቹ በሚገኙበት ቦታ ላሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም የገቢ ምንጭ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡
በስልጠናዉ የተሳተፉ ሰልጣኞችም ስልጠናዉ በዘርፉ ያለባቸዉን ክፍተት እና የበለጠ ከመሳሪያዎቹ ጋር እንዲተዋወቁ የረዳቸዉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ስልጠናዉን የሚሰጡት ከሺሚትዙ ኩባኒያ የመጡ እና እንዲሁም በሀገር ዉስጥ የኩባኒያዉ ወኪል አከፋፋይ የሆኑ የቴክኒክ ባለሙያዎች እንደሆኑ ተገልጿል ፡፡