News
ኢንስቲትዩቱ የዓለም የሥነ-ልክ ቀን በደማቅ ሁኔታ አከበረ

ኢንስቲትዩቱ የዓለም የሥነ-ልክ ቀን በደማቅ ሁኔታ አከበረ
ቅዳሜ ግንቦት 13 ቀን 2008 ዓ.ም በዓለም ለ141 ኛ በሀገራችን ለ7ኛ ጊዜ የሚከበረዉ የዓለም የሥነ-ልክ ቀን የአንስቲትዩቱ ደንበኞች፣ ባለድርሻ አካላት ፣የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡
በዓሉን በንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወድወሰን ፍሰሃ ሲሆኑ ዘርዘር ባለ ሁኔታ ስለ በዓሉ አጀማመር እና አላማ ገለፃ አድርገዉ የበአሉን ዝግጅት አስጀምረዋል፡፡ የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሡ ሲሆኑ ለዓሉ ታዳሚዎች የተቋሙ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን በመግለፅ ወደፊትም የሀገራችንን የሥነ-ልክ ፍላጎት ለማሟላት ብዙ መሥራት እንዳለበት በንግግራቸዉ ገልፀዋል፡፡
የዓለም የሥነ-ልክ በዓል የሚከበረዉ እ.አ.አ ግንቦት 20 ቀን 1875 ዓ.ም 17 የዓለም ሀገሮች ወጥ የልኬት ሥርዓት በዓለም ላይ እንዲኖር በመስማማት መሠረት የጣሉበት ቀን ነዉ፡፡በዓለም ላይ ወጥ የልኬት ሥርዓት የማይኖር ከሆነ የጋራ ገበያ ያላትን ዓለም መፍጠር ስለማይቻል ይህንን ለመፍታት ጉልህ ሚና ነበረዉ፡፡