News
ኢንስቲትዩቱ በሙቀትና ግፊት የዓለካክ ዘርፎች ዓለም አቀፍ እውቅና ተራዘመለት

የጀርመኑ ዕውቅና ሰጪ ተቋም ዳክስ /DAkkS/ ለኢንስቲትቱ የላከው መረጃ እንደሚገልፀው ከተቋሙ የመጡት ባለሙያዎች የኢንስቲትዩቱን ላብራቶሪዎች በጎበኙበት ወቅት የተመለከቷቸው የጥራት ሥራ አመራር ማኔጅመንት አሰራሮች እና ኢንስቲትዩቱ ከዚህ በፊት ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያገኘባቸው ዘርፎች የሚፈልጉትን ሂደቾች ጠብቆ መስራቱ እውቅናውን እንዲያራዝሙ እንዳስቻላቸው ገልፀዋል፡፡
ከተገኘውም የእውቅና መራዘም በተጨማሪ በሙቀትና ግፊት የዓለካክ መስኮች ወሰን የማስፋት ስራዎች ተሰርቷል፡፡ በዚሁ መሰረት በሙቀት የአለካክ መስክ ከዚህ በፊት ዝቅተኛ የመለካት ወሰን እስከ -400C የነበረው አሁን እስከ -800C ማድረስ ተችሏል፡፡ በምርጥ የአለካክ አቅም ለሙቀት ሬዚስታንስ ቴርሞሜትር “Temperature Resistance thermometers” ከ2000C እስከ 6600C ከዚህ በፊት 0.60 k የነበረውን በእጥፍ በማሻሻል ወደ 0.30 k ድረስ የመለካት አቅም
ማሳደግ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ በብርጭቆ ውስጥ ያለ ፈሳሽ ሙቀት መለኪያ (Liquid in glass thermometers) ከ2000C እስከ 3600C፣ በዳይሬክት ሪዲንግ ኤሌክትሪካል ቴርሞሜትር (Direct reading electrical thermometer) ከ2000C እስከ 660C እና በሜካኒካል ቴርሞሜትር (Mechanical(dial) thermometers) ከ2000C እስከ 4000C ከዚህ በፊት 0.60k የነበረውን የአለካክ አቅም ወደ 0.30k ድረስ ለማሻሻል ተችላል፡፡
በግፊት የአለካክ መስክ ከዚህ በፊት በዓለም አቀፍ ዕውቅና ወሰን ውስጥ ያልነበረ አብሶሊት ፕሬዠር (Absolute pressure Pabs) “ ከ (0.14 bar) ወደ (70 bar gas medium) በማሳደግ ዕውቅና ማግኘት ተገኝቷል፡፡ ከዚህ በፊት ዕውቅና ባላቸው ላይም የአለካክ ወሰን ተሻሽሏል፡፡ በዚህም መሰረት በጋስ ሚዲየም (Gas medium) ከዚህ በፊት ከ2 ባር እስከ 140 ባር የነበረው ወደ 0.014 ባር አስከ 140 ባር የተሻሻለ ሲሆን በምርጥ የአለክክ አቅም ከ(0 bar) እስከ (140 bar) ከዚህ በፊት (0.8 mbar) እስከ (56 mbar) የነበረውን አሁን ከ(0.10 mbar) እስከ (25 mbar) ተሻሽሏል፡፡ እንዲሁም በኦይል ሚዲየም (Oil medium) ከ(0.5 bar) እስከ (60 bar) ለዚህ በፊት (54 mbar) የነበረው ምርጥ የአለካክ አቅም ወደ (42 mbar) ለመሻሻል ተችሏል፡፡