News
ኢንስቲትዩቱ ከህዝብ ክንፍ እና ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ

ኢንስቲትዩቱ ከህዝብ ክንፍ እና ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ

ኢንስቲትዩቱ መስከረም 28/2008 በኔክሰስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ከህዝብ ክንፍ እና ባለድርሻ አካላት ጋር ለግማሽ ቀን የቆየ ዉይይት አካሄደ፡፡ በዉይይቱ ላይም ከተቋሙ ጋር ቀጥታ የስራ ትስስር ያላቸዉ ማህበራት፤የግል እና የመንግስት ተቋማት እንዲሁም ዋነኛ ባለድርሻ አካላት (potential customers) ተሳታፊ ሆነዋል፡፡


አቶ ወንድወሰን ፍሰሃ የ ኢንስቲትዩቱ ዋና ደይሬክተር የ መክፈቻ ንግግር ካደረጉ በኋላ በአቶ ሙልጌታ ደርበዉ የሳይንሳዊ ሥነ-ልክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ስለ ተቋሙ ስራዎች፤ስለ ህዝብ ክንፍ እና ባለድርሻ አካላት ሚና፤ በአጠቃላይ ኢንስቲትዩቱ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ሊኖረዉ ስለሚገባ የስራ ሁኔታ ገላፃ ተደርጓል፡፡ በገለፃዉ ላይ በዋናነት ተቋሙ በሀገሪቱ የካሊብሬሽን አገልግሎት መስጠት፤በካሊብሬሽን ዘርፍ ለሚሰማሩ ልማታዊ ባለሃብቶች ድጋፍ ማድረግ፤በሳይንስ መሣሪያዎች ዘርፍ የስልጠናና ምክር አገልግሎት መስጠት፤በሣይንስ መሳሪያዎች ጥገና፤ተከላና ኮሚሺኒንግ አገልግሎት መስጠት እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መስጠት አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ እና ባለድርሻ አካላትም የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ማግኘት እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡


በተሰጠዉ ገለፃ ላይም ዋና ዳይሬክተሩ ከተሳታፊዎች ጥያቄ እና ገንቢ አስተያየት በመቀበል የተቋሙ ሥራ አመራር አካላት እና እራሳቸዉ ምላሽ ሰጥተዉባቸዋል፡፡ ከተሳታፊዎች ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል የካሊብሬሽን አገልግሎት ዉስንነት፤የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች እጥረት፤የባለሙያዎች ብቃት፤የስልጠናና ምክር አገልግሎት ጉዳዮች ሲሆኑ ከተሰጡት ገንቢ አስተያየቶች መካከል ተቋሙ ለጋነዲ መታሰቢያ ፤ለራስ ደስታ እና ለሚኒሊክ ሆስፒታሎች ራሳቸዉን ችለዉ የጥገና ዩኒት(workshop)እንዲያቋቅሙ የተሰጠዉ አገልግሎት የሚበረታታ እና ቀጣይነት ሊኖረዉ የሚገባ ተግባር እንደሆነ፤ዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስርአት ተጠቃሚ መሆን እና ለደንበኞችም በዛ የተቃኘ አገልግሎት መሰጠት እንዳለበት እና አሁንም የአቅም ግንባታ ላይ በሰፊዉ መሰራት እንዳለበት ተነስቷል፡፡ 


ዋና ዳይሬክተሩ በተነሱት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ላይ ከተቋሙ ሥራ አመራር አካላት ጋር በመሆን ምላሽ ሰጥተዉባቸዋል፡፡ በምላሻቸዉም ኢንስቲትዩቱ በሀገሪቱ ያለ ብቸኛ የካሊብሬሽን አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም እነደሆነና ጫናዎች እንደሚበዙበት ይሄንንም ለመቅረፍ የግል ተቋማት በዘርፉ መሰማራት እንዳለባቸዉና የተቋሙ ሚናም ሙያ