News
ኢንስቲትዩቱ ሰራተኞቹን በቀጣይ አምስት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ አወያየ

የተቋሙ አስተዳደር እና ሰራተኞች መስከረም 24/ 2008ዓ.ም ኮተቤ በሚገኘዉ የኢንስቲትዩቱ መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያለፈዉን አምስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ ትግበራ፣ አፈፃፀም እና የሚቀጥሉትን አምስት አመታት እቅድ ላይ ተወያዩ፡፡ ውይይቱን የመሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን ፍሰሓ ሲሆኑ ዳይሬክተሩ ዉይይቱን ሲጀምሩ እንደገለፁትያለፈዉን እቅድ አፈፃፀም እና የቀጣዩን እቅድ ማወያየት ያስፈለገዉ ሁሉም ዜጋ በዕቅዶቹና አፈፃፀማቸው ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲይዝ እና ለእቅዱ ተፈፃሚነት የእራሱን ድርሻ እንዲወጣ ነዉ ፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ያለፈዉ አምስት አመት (2002-2007) የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈፃፀምን በተመለከተ 10.1 በመቶ ተቀራራቢ እድገት በተከታታይ የተመዘገበበት፤የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ ከፍ ያለበት፤በማህበራዊ፤መሰረተ ልማት እና በሌሎች ዘርፎች ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ዉጤት የተመዘገበበት እንደነበር ተገልፃል፡፡ በአንፃሩ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኤክስፖርትና በግብርና ዘርፎች የተጠበቀዉን ያህል ዉጤት ሊመዘገብ አለመቻሉ እና በቀጣይም የሞት ሽረት ትግል በማድረግ በዘርፉ ላይ እመርታዊ ለውጥ መምጣት ግድ እንደሆነ አስቀምጠዋል፡፡

የቀጣይ አምሰት አመት (2008-2012) የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በተመለከተ፤ እቅዱ ካለፈዉ የእቅድ ዘመን ትምህርት የተወሰደበትና የነበሩትን ክፍተቶች ለመሙላት እንደሚሰራ ተገልፃል፡፡ በእቅዱ ዉስጥም ልዩ የትኩረት መስኮች የተካተቱ ሲሆን እነሱም የግብርና፤ማኑፋክቸሪንግ፤ኤክስፖርት፤የሰዉ ሃብት ልማት እና የአከባቢ ጥበቃ እንደሆኑ ተገልጧል፡፡ ዕቅዱ ለሰራተኞች ከቀረበ በኃላ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ሰራተኞቹም ግልፅ እንዲሆኑላቸው በፈለጉባቸው ጉዳዮች ጥያቄ አቅርበውና ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶባቸው የውይይቱ ፍፃሜ ሆኗል፡፡