News
ኢንስቲትዩቱ ከአጋር አካላት ጋር በመሆን በህጋዊ ሥነ-ልክ ላይ ስልጠና እየሰጠ ነዉ

ኢንስቲትዩቱ ከአጋር አካላት ጋር በመሆን በህጋዊ ሥነ-ልክ ላይ ስልጠና እየሰጠ ነዉ

ዛሬ ከተጀመረ ሁለተኛ ቀኑን የያዘዉ ይህ ስልጠና በህጋዊ ሥነ-ልክ ላይ የሚያተኩር ተግባራዊ ስልጠና ሲሆን ከኬኒያ በመጡ የዘርፉ አማካሪ ባለሙያዎች ከብሔራዊ የሥነ-ልክ ኢንስቲትዩትና አዲስ አበባ ፖሊ ቴክኒክ ለተዉጣጡ ባለሙያዎች እና መምህራኖች እየተሰጠ የሚገኝ ነው፡፡
አቶ ሙልጌታ ደርበዉ በብሔራዊ የሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የሳይንሳዊ ሥነ-ልክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደገለፁት የኢንስቲትዩታችን ዋነኛ እና ተቀዳሚ ዓላማዉ ብሔራዊ የአለካክ ስርአቶችን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡ የዘመናዊ አለካክ ስርአት ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል በመሆኑ፤ በተለይም ደግሞ በህጋዊ ሥነ-ልክ ዙሪያ ያሉብንን ክፍተቶች በመለየት የአሁኑን አይነት አጫጭር እና ረጃጅም ስልጠናዎችን ከአጋር አካላት ጋር በማዘጋጀት ክፍተቶቹን ለመሙላት እንሰራለን ብለዋል፡፡ 


ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አክለውም አሁን እየተሰጠ ያላዉን ስልጠና ኢንስቲትዩቱ ከንግድ ሚኒስቴር፤ ከ ጂ አይ ዜድ እና ከአዲስ አበባ ፖሊ ቴክኒክ ጋር በመተባበር በሥነ-ልክ ዙሪያ የሚሰሩ እና የሚያማክሩ ባለሙያ ከኬንያ በመጋበዝ ለሁለት የኢንስቲትዩታችን የሳይንሳዊ ሥነ-ልክ ባለሙያዎች እና ለሶስት የአዲስ አበባ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመጡ መምህራኖች ስልጠናው እየተሰጠ ነዉ፡፡ 
አቶ ሙልጌታ አያይዘዉም እነዚህ ስልጠናዉን እየወሰዱ ያሉት ሰልጣኞች ስልጠናዉን ካገኙ በኋላ በህጋዊ ሥነ-ልክ ዘርፍ ያለዉን ክፍተት በማስተማር ፤ሌሎችን በማሰልጠን እና ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ ክፍተቱን እንደሚሸፍኑ ይታመናል ፡፡
ሚስተር አይሳክ ማጎንዱ በኬንያ የህጋዊ ሥነ-ልክ የግል አማካሪ እና ባለሙያ እንደነገሩን አሁን እየተሰጠ ያለዉ ስልጠና በተግባር የተደገፈ እንደሆነና በተዋረድ እስከታች ድረስ ይህን መሰል ስልጠና ከተሰጠ በሀገሪቱ ዉስጥ ፍትሐዊ፤ሚዛናዊ እና ዘመናዊ የልኬት ስርአት በቀላሉ መዘርጋት ይቻላል ብለዋል፡፡


በስልጠናዉ ላይ ተሳታፊ የሆኑት እና ከአዲስ አበባ ተግባረ እድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተሳተፉት መምህር አቶ ሰለሞን አሰግደዉ እንደገለፁት የአሁኑን አይነት ስልጠና ከዚህ በፊትም ወደ ኬኒያ ሄደዉ እንደወሰዱና አሁንም እየተሰጠ ያለዉ ስልጠና በዘርፉ ያለዉን ክፍተት ለመሸፈን አስፈላጊ እንደሆነ እንዲሁም ዘመናዊ የልኬት ስርአት ለመፍጠር ቁልፍ ተግባር ነው፡፡
ስልጠናዉ መስከረም 3/2008 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን እስከ መስከረም 15/2008 እንደሚቀጥልና በቀጣይም ኢንስቲትዩቱ እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን ተመሳሳይ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡