News
ኢንስቲትዩቱ መልካም አፈፃፀም ላመጡ የስራ ሂደቶች እና ግንባር ቀደም ሰራተኞች እዉቅናና ሽልማት ሰጠ

ኢንስቲትዩቱ መልካም አፈፃፀም ላመጡ የስራ ሂደቶች እና ግንባር ቀደም ሰራተኞች እዉቅናና ሽልማት ሰጠ ፡፡

በዛሬዉ እለት ኢንስቲትዩቱ ኮተቤ በሚገኘዉ ግቢ ባለፉት ስድስት ወራት በስራቸዉ አመርቂ ዉጤት ላመጡ የስራ ሂደቶች እና መልካም አፈፃፀም ላሳዩ ግንባር ቀደም ሰራተኞች እዉቅና እና ሽልማት ሰጠ፡፡ ሶስት (3) የስራ ሂደት እና ሰላሳ ዘጠኝ (39) ግንባር ቀደም ሰራተኞች የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት እንዲሁም ለእያንዳንዱ ግንባር ቀደም ሰራተኛ የ አምስት መቶ ብር (500) ቦንድ ሽልማ ት ከኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ከአቶ ወንደወሰን ፍሰሃ እጅ ተቀብለዋል፡፡ በተጨማሪም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሸለመዉ ዋንጫ ኢንስቲትዩቱ የሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋም በመሆኑ እና ለሽልማቱም አስተዋፅኦ በማድረጉ ዋንጫዉ በዙር ወደ ኢንስቲትዩቱ መጥቷል፡፡
አቶ ወንድወሰን ፍሰሃ የኢንሰቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በስነ - ስርአቱ ላይ እነደገለፁት የግንባር ቀደም መመልመያ መስፈርት ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር በወረደዉ መመሪያና መስፈርት ከየስራሂደቶቹ በስራቸዉ ግንባር ቀደም የሆኑ ሰራተኞችን ተመልምለዉ ሊሸለሙ ችሏል ፡፡ አቶ ወንደወሰን አክለዉ እንደገለፁት ግንባር ቀደም ማለት በስራዉም ይሁን በአመራር ቀድሞ የተገኘ እና በመረጃ የተደገፈ ለዉጥ ያመጣ ሰራተኛ እንደሆነ ገልፀዋል ፡፡ የግንባር ቀደም መፈተሻ ሜዳዉም የሰራተኛዉ የስራ ገበታ ብቻ እንደሆነ አስምረዉበታል፡፡


በተመሳሳይ ከ አንድ እስከ ሶስት በመዉጣት የተሸለሙት የስራ ሂደቶች በአመቱ የአቀዱትን እቅድ ግብ ከመምታት አኳያ እንደሆነ ዋና ዳይረክተሩ ለተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ከ አንድ እስከ ሶስት በመዉጣት ዋንጫ የተሸለሙት የስራ ሂደቶች የእቅድ ዝግጅት እና ክትትል የስራ ሂደት ፤ የሳይንስ መሳሪያዎች ጥገና የስራ ሂደት እና የ ኦዲት አገልግሎት የስራ ሂደቶች ናቸዉ፡፡ 
ዋና ዳይሬክተሩ በአጠቃላይ እዉቅና እና ሽልማት አሰጣጥ ላይ ከተሳታፊዎች አስተያየት በመቀበል በአስተያየቶቹ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ከተሳታፊዎች መሀከል ከተነሱት አስተያየቶች መካከል ግንባር ቀደሞች የተመረጡበት ስራዎች የተለዩ እና ከመደበኛ ስራ ዉጪ አለመሆናቸዉ፤ የተለያዩ በግምገማ በደንብ ያልጠሩ የአመራረጥ ሂደቶች ታርመዉ የተሻለ የፈጸሙ ሠራተኞችን ብች መምረጥ እዲቻል የሥራ ሂደት መሪዎችና ሠራተኞቹም ተሳትፎ እንዲያጎለብቱ ተገልፀዋል፡፡በመጨረሻም የፎቶ ስነ ስርአት በማከናወን ፕሮግራሙ ተጠናቋል ፡፡