News
ኢንስቲትዩቱ በሥነ-ልክ ዘርፍ የውስጥ አቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጠ

                              ኢንስቲትዩቱ በሥነ-ልክ ዘርፍ የውስጥ አቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጠ
ብሔራዊ የሥነ ልክ ኢንስቲትዩት በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 194/2003 ከተቋቋመ ጀምሮ፤የሀገሪቱን የሥነ-ልክ ፍላጎት ያሟላ፡አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለውና በአፍሪካ ግንባር ቀደም ተዓማኒ ብሔራዊ የሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት መሆንን ራዕይ አድርጎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡


ይህ ተቋማዊ ራዕይ ይሳካ ዘንድ በኢንስትቲዩቱ በኢንዱስተሪያዊ እና ሳይንሳዊ ሥነ-ልክ የስራ ክፍሎች ውስጥ በመሥራት ላይ የሚገኙ ባለሙያዎችን የውስጥ አቅም የመገንባት ሥራ ለተከታታይ ዓመታት ሲሰራ ቆይቷል፡፡በዚህ ዓመትም ከነሃሴ 10-17 2007 ዓ.ም በአዳማ ከተማ የሥነ-ልክ ሣይንስን አስመልክቶ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን ፍስሃን ጨምሮ ነባር የዘርፉ ባለሙያዎች ሥልጠናውን የሰጡ ሲሆን ሥልጠናው በተግባር የተደገፈ ነበር፡፡