ዜናዎች
አንስቲትዩቱ ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር የጋራ መስራት ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

አንስቲትዩቱ ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር የጋራ መስራት ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

የስምምነቱ ዋና ዓላማ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትን የራሱ የመሳሪያዎች ጥገና እና የካሊብሬሽን ወርክሾፕ እንዲያቋቁም ማገዝ ነው፡፡ ይህም የምርምር ማዕከሉን የልኬት ደረጃዎችን በማጠናከር ብሔራዊ የምርምር ስርዓቱን ተወዳዳሪ ለማድረግ ይረዳል፡፡ 
በስምምነቱ መሰረት ብሔራዊ የሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት የምርምር ኢንስቲትዩቱ የራሱን የጥገና እና የካሊብሬሽን ወርክሾፕ ለማቋቋም የሚረዱትን ሂደቶች በሙሉ ያከናውናል፡፡ ከዚህም መካከል የምርምር ኢንስቲትዩቱን የመለካት አቅም ጥናት፣ በሰነዶች ላይ የተመሰረተ የካሊብሬሽን ፍላጎት ጥናት፣ የባለሙያዎች ብቃት ዳሰሳ እና ለምርምር ኢንስቲትዩቱ ወርክሾፖቹን ለማቋቋም የሚረዱ መረጃዎች በማጠናከር ተገቢውን ምክር ማስቀመጥ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ብሔራዊ የሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት በህግ ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት መካከል ለኢንዱስትሪው የሥነ-ልክ ጽንስ ሃሳብና የተግባር ሥልጠናና የምክር አገልግሎት በመስጠት የራሳቸውን የውስጥ ካሊብሬሽን ላቦራቶሪዎችን እንዲያቋቁሙ እገዛ የማድረግ እና የሳይንስ መሣሪያዎች ተጠቃሚ ተቋማት የራሳቸው የሳይንስ መሣሪያዎችን ጥገና ወርክሾኘ እንዲያቋቁሙ የሥልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ ማድረግ ይገኙበታል፡፡

ስምምነቱን ተቋማቱን በመወከል የብሔራዊ የሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን ፍሰሐ እና የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፋንታሁን መንግስቱ ፈርመዋል፡፡