የካሊብሬሽን አገልግሎት የሚሠጠው በ3 ዓይነት መልኩ ሲሆን ይኽውም ወደ የሚሰጡ አገልግሎቶች ዋና ገጽ ተመለስ

 

1.  የላብራቶር ውስጥ ካሊብሬሽን

2.  የመስክ ካሊብሬሽን እና

3.  ተንቀሳቃሽ ካሊብሬሽን ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የላብራቶር ውስጥ ካሊብሬሽን አገልግሎት የሚሰጠው ከፍተኛ የካሊብሬሽን አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው ሲሆን ሌሎች ትናንሽ ካሊብሬሽን ለሚፈልጉ ወደ ኢንስቲትዩቱ ላብንቶሪ ማምጣት ለለማይችሉ መሣሪያቸውን ደግሞ ኢንስቲትዩቱ ተንቀሳቃሽ ካሊብሬሽን ላብራቶሪውን በመያዝ ቦታው ድረስ ሄዶ አገልግሎት ይሠጣል ተንቀሳቃሽ የካሊብሬሽን ላብራቶሪ ውስጣቸው የያዙት መኪኖቻችን ቀድመው ቀጠሮ በተያዘላቸው መሠረት በመላ ኢትዮጲያ በመዘዋወር አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ ፋብሪካዎችና ሌሎች የነዚህ ላብራቶሪዎች ይጠቀማሉ፡፡

ሀገራዊ የልኬት ደረጃ ተዋረድ መጠበቅ
1
የኤሌክትሪክ ልኬት ስታንዳርድ

 

በቀጥተኛ የኤሌክትሪክ አለካክ (ዲሲ)ከ1.018ቮልቴጅ ± 0.5 ፒፒኤም እና በቀጥተኛ የኤሌክትሪክ አለካክ  የማነፃፀሪያ ስታንዳርድ ከ 10ቮልት ±1.1ፒፒም የቮልቴጅ ካሊብሬሽን ሀገር አቀፍ ማነፃፀርያዎች ናቸው፡፡

ከ0.001ዋት እስከ 1ሜጋ ዋት ድረስ  የከረንንት እርከን ተዋረድ ይጠበቃል፡፡

2
የግዝፈት መለኪያ ስታንዳርድ

ሀገር አቀፉ የግዝፈት ልኬት ስታንዳርድ ለ E2 ከ1ሚ.ግ እስከ 10ኪ.ግ ሲሆን ለሌሎቹ F1 ነው፡፡

3
የርዝመት መለኪያ ስታንዳርድ

 

የርዝመት መለኪያ ስታንዳርድአንዱ ሴት 116 ነጠላ ስብስቦች ከ 0.5 ማይክሮ ሜትር እስከ 500 ሚሊ ሜትር ኖሚናል ቫልዩ የያዘ ሲሆን ይህንኑ ከኬጅ ብሎክ ጋር በመጠቀም ከ 0.5 ማይክሮ ሜትር እስከ 900 ሚሊ ሜትር ካሊብሬት ማድረግ ይቻላል፡፡

Temperature measurement standard= የሙቀት መለኪያ ስታንዳርድ

4
የሙቀት መለኪያ ስታንዳርድ

ሀገር አቀፍ የሙቀት ካሊብሬሽን ስታንዳርዶች በፕላቲኒየም ሬዚስታንስ ቴርሞሜትር ከ-40 እስከ 660OC እና በኖብል ቴርሞካፕልስ ከ660 እስከ 1200 OC ነው፡፡

5
የአዮናይዜሽን ጨረራ ስታንዳርድ

ሀገር አቀፉ የአዮናይዝሽን ጨረራ የሚለካው Cs-137  ስታንዳርድ መሰረት ነው፡፡