ስለ ኢንስቲቲዩቱ

ብሔራዊ የሥነ-ልክ ኢንስቲዩት (ብሥኢ) ሀገራዊ የልኬት ደረጃ ተዋረድን ለመጠበቅና ለማሰራጨት የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ነው፡፡ ኢንስቲትዩቱ የካሊብሬሽን፣ የስልጠና እና የምክር አገልግሎቶችን በሥነ-ልክና በሳይንስ መሳሪያዎች ዘርፍ ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም የሳይንስ መሳሪያዎች ጥገና አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ነው፡፡

ዓላማ

 

  • ከአለም አቀፍ ሥነ-ልክ ስርዓት ጋር የተጣጣመ ብሄራዊ የሥነ-ልክ ስርዓትን የመዘርጋትና  በዘርፉ የቴክኖሎጂ ሽግግርን የማምጣት፤
  • የአገሪቱን ብሔራዊ የመለኪያ ኢታሎኖችና የተመሰከረላቸውን የማመሳከሪያ ስረቶች ከዓለም አቀፍ የመለኪያ ኡታሎኖች ጋር ለማመሳከር፣ ለመጠበቅና የአገሪቱን ብሔራዊ የመለኪያ ኢታሎኖችና የተመሰከረላቸውን የማመሳከሪያ ስረቶች ከዓለም አቀፍ የመለኪያ ኢታሎኖች ጋር ለማመሳከር፣ ለመጠበቅና ለማሰራጨት የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት የመዘርጋትና የመተግበር፤
  • በሥነ-ልክ ዘርፍ የትምህርትና የምርምር ተግባሮችን የመደገፍ፤
  • የሳይንሰ መሣሪያዎችን ጥገና ብሔራዊ አቅም መገንባትና የጥገና አገልግሎት መስጠት፡፡
  • የሳይንስ መሣሪያዎች የቴክኒክ ፣ የሥልጠና፣ የምክርና የመረጃ አገልግሎቶችን በመስጠት የሳይንስ መሣሪያዎች ተጠቃሚዎች ተግባሮቻቸውን በብቃት እንዲከናወኑ መደገፍ ነው፡፡

 

ተልዕኮ

 

ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸውን የአሠራር ልምዶችን መሠረት ያደረገ ብሄራዊ የአለካክ ሥርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን ዘመናዊ የአለካክ ሥርዓት ተጠቃሚ አንዲሆን ማስቻል፡፡

ራዕይ

 

የሀገሪቱን የሥነ-ልክ ፍላጎት ያሟላ፣ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለውና በአፍሪካ ግንባር ቀደም ተዓማኒ ብሔራዊ የሥነ-ልክ ኢንስቲትዩት መሆን፣

የስራ አመራሩን ማግኘት ይፈልጋሉ?
NAME: Wondwosen Fisseha
 
Director General
 
NAME: Fikreab Markos       
 
Technical Advisor
NAME: Mulugeta Derebew             
 
Director, Industrail Metrology
NAME: Gizache Betru
 
Director, Scientific Metrology
 
NAME: Abebayehu Mamu     
 

Director, Training and

consultancy Service

NAME:           
 

Head, Scientific Equipment

Maintenance Service

NAME: Dechasa Gurumu
 

Head, Communication and

Public Relation Service

 
 
 
NAME: Shiferaw Tadese   
 

Head, Audit Service

NAME: Sirgawi Kebede  
 

Head, Finance and
Supply Service

 

NAME: Gemechu Amente
 

 Human Resource Development

and Administration Service

 
NAME: Kokebe Lema
 

Heade, Information Technology
& library Service

 

NAME: Sintayeu Wondimu
 

Head, Plan and Programing Service